Sheger FM 102.1 - Addis Abeba....
African Music, Ethiopia
SHEGER FM 102.1 'yenanetew radio' is the first private radio station in
Ethiopia. we are proud to be Ethiopians...and we love our country more than
anything! hear us live on www.shegerfm.com
Founding date 2000 e.c
an 18 hour all day broadcasting of news, features, programs and music. We're
also re-streaming selected programs in our internet and dedicated phone
numbers from mid night to morning to make it 24 hrs online streaming.
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ መስከረም 23 ቀን 2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ
ጣቢያ ነው፡፡ ይህ ከአዲስ አበባ በ250 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ፕሮግራም እንዲያሰራጭ ፈቃድ አግኝቶ የረጅም ጊዜ የሬዲዮ
ሥራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን
ሊያተርፍ ችሏል፡፡ ሸገር 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ
ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡ የሸገር ዓላማ ከወገናዊነት የነፃ ትክክለኛ የሕዝብ ድምፅ መሆን፣ ሥነ ምግባርን የጠበቀ
የጋዜጠኝነት መርህን መከተልና የተሣካለት የኢንፎቴይመንት (information & entertainment) ሬዲዮ ጣቢያ መሆን
ነው፡፡ ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና
ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡
Facebook
Twitter
Radio's Website